Amharic - አማርኛ

DSHS አግልግሎቶችን በመረጡት ቋንቋ ያቀርባል። እኛ ስለሚናቀርባቸው የአገልግሎት ዓይነቶች የበለጠ ለማወቅ፥ እባክዎትን ከሰኞ እስክ ዓርብ በ8 a.m. እና 5 p.m. መካከል ባሉት ጊዜያት በዚህ ይደውሉ 800-737-0617።

ድምፅ የሚቀዳው ጋር ሲደርሱ፥ እባክዎትን በስልክ ቁጥሪዎ በሚናገሩት ቋንቋ መልክት ያስቀምጡና እኛ ደግሞ በመስመሩ ላይ በአስተርጓሚ ጥሪዎን እንመልሳለን። መስማት ለሚሳናቸው፥ መስማት ለሚያስቸግራቸው፥ መስማትና ማየት ለተሳነቸውና የመናገር ውስንነት ላለባቸው ደንበኞች ወይም ግለሰቦች፥ እባክዎትን በመረጡት የኮሙንከሸን አገልግሎት አቅራቢዎ በኩል በዚህ ያግኙን 360-111-2222።
DSHS ምን ዓይነት አገልግሎቶችን ያቀርባል?

• ምግብ፥ ጥሬ ገንዘብ፥ መኖሪየያ ቤትና የጤና ጥቅማጥቅሞች: 877-501-2233
• የልጆች ድጋፍ፡ 800-442-5437
• የአዋቂዎች እንክብካቤ: 877-734-6277
• የአዋቂዎች ጥበቃ: 866-363-4276
• ውስንነት ላለባቸው ድጋፍ: 800-248-0949
• ሙያዊ ማገገሚያ: 800-637-5627

የሚፈልጉትን አግልግሎቶች ማግኘትዎን ለማረጋገጥ፥ ከእርስዎ ጋር እንዲንነጋገር የሚያግዙን፥ ዶኩሜንቶችን የሚተረጉሙ፥ ዶክሜንቶችንም በትልቁ አሳትሞ ወይም በብሬል የሚያቀርቡ፥ የተፃፉትን ነገሮች በድምፅ ግልባጭ እና ሌሎችን የሚያቀርቡ አስተርጓሚዎችን እናመቻቻለን።

የሲቭል መብቶች ሕግ አንቀፅ VI DSHS ዘርን፥ ቀለምን ወይም የመጡበትን ሀገር መሠረት በማድረግ እንዳያዳላ ይከለክላል። በመረጡት ቋንቋ አገልግሎቶችን ጠይቀው ካላገኙ፥ ወይም DSHS በእርስዎ ላይ አድሎ እንደሚያደርግ ከተሰማዎት መሠረታዊ አገልግሎቶችን በዚህ ያግኙ 800-737-0617 ወይም ቅሬታዎን በኢሜል ይላኩ iraucomplaints@dshs.wa.gov.

በእነዚህ መስሪያቤቶችም የአድሎ ቅሬታዎን ማቅረብ ይችላሉ፡
የወሽንግተን ስቴት ጠቅላይ ዐቃቤ-ሕግ ጽ/ቤት (800-551-4636)
የዋሽንግተን ስቴት ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (800-233-3247)
U.S. የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ (800-368-1019).